tg-me.com/nibab_lehiwot/159
Last Update:
በራሴ ውስጥ እየጠፋሁ እንዳለሁ ይሰማኛል። ከራስ ውስጥ ራስን ማጣት ልለው እችላለሁ። መሆን የምፈልጋት እኔን እየሆንኩ እንዳልሆነ ይታወቀኛል ግን ደግሞ የምፈልጋትን እኔን ለመሆን ምንም ጥረት አላደርግም። እንደምችል ይነግረኛል ግን............(ቃል አጠረኝ😥)በቃ
ከቀን ምሽትን ከ ፀሀይ ዝናብን የምመርጠው በምክኒያት ነው። በምሽት ማንም እንባየን አያይም ተፈጥሮ እንዳያይ ትከለክለዋለችና ለእኔ ግን የውስጤን ህመም ጨርሶ ባያድንልኝ እንኳን የታመቀውን ስቃይ ያስተነፍስልኛል። ማንም አየኝ አላየኝ አልሳቀቅም፣ ሰሙኝ አልሰሙኝ አልጨነቅም።በቃ ..........
በዝናብም እንዲሁ በጠብታው ከበሰበሰው አይኖቼ ውስጥ የሚወጣውን እንባ ማንም ሊያስተውለው አይችልም። በፈገግታ ውስጥ የተሸፈነ ትልቅ እንፋሎቴንን ከቀዝቃዛው የሰማይ ውሃ ጋር ተቀላቅሎ እንዲወርድ ያለማንም ከልካይ እፈቅድለታለሁ። ለትንሽ ሰዓታትም ቢሆን እፎይ እላለሁ።
አላውቅም ብዙ ሰወች እንደዚህ አይነት ህመም ውስጥ እንዳሉ ይሰማኛል። እንደሚቻል እያወቁ ማድረግ አለመቻል፣ ራስን መውቀስ፣ ዝቅ ማድረግ፣ ከራስ ጋ መጣላት፣ መታመም ከዛ በፈገግታ መሸፈን፣ ሰላምን መፈለግ፣ ርቆ መጥፋት መመኘት፣ ለምን የሚሉ ብዙ ጥያቄወች፣ መጠራጠር፣ ብዙ በጣም ብዙ ነገሮች ያመሳስሉናል።
ብቻ ግን ከዚህ ለመውጣት ይሄንን አድርጉ ብየ አልመክራችሁም እኔም እዛ ህመም ላይ ነኝና።😔😔😔😔
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
BY ሕይወትን - በገፅ

Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/159